ዮናታን ተስፋዬ ስድስት አመት ከስድስት ወር ቅጣት ተወሰነበት::

ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ውሎው በሽብር ወንጀል የተጠረጠረው ዮናታን ተስፋዬ ስድስት አመት ከስድስት ወር ቅጣት ወስኖበታል፡፡

ጠበቃ ሽብሩ በለጠ ስድስት የቅጣት ማቅለያዎችን ለፍ/ቤቱ በፅሁፍ ማስገባታቸውን በገለፁበት በዚህ ችሎት ከስድስቱ ቅጣት ማቅለያዎች የበጎ ስራ ስራዎችን በነፃ መስራቱ፣ በበጎ ፍቃደኝነት የደም ልገሳ ማካሄድ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ብቻ መቀበሉን የገለፀው ፍርድ ቤቱ የተጠቀሱትን ብቻ ማቅለያዎች በመቀበል ተከሽ ዮናታን ተስፋዬ እጁ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡
ሽብርተኛ ማን ነው? ማንን ነው የሚያበረታታው? ሽብር ምንድን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎችን እና በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የነበረው ተቃውሞ በመልካም አስተዳደር እጦት ችግር መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስቴሩ መገለፃቸውን በድጋሜ በማቅረብ ይግባኝ ልንጠይቅ እንችላለን ያሉት ጠበቃ ሽብሩ ይህንን ለማድረግ የቅጣት ውሳኔውን ዝርዝር ከተመለከትን እና በየትኞቹ ላይ ይግባኝ እንደምንጠይቅ ከከደንበኛዬ ዮናታን ጋር ከተወያየን በኋላ ነው ብለዋል፡፡ ዮናታን ተስፋዬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም እጁ ተይዞ በዚሁ ፍ/ቤት ሲከታተል መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ፕሮጀክታችን ዬናታንን የፍርድ ሂደትን ሲከታተል ቆይቶ ዋና ዋና የፍርድ ቤት ሂደቱን የሚያሳይ ማጠቃለያ ከጥፋኝነት ከብይኑ አስቀድሞ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ የዮናታን የ1 አመት ከ6 ወር የፈጀ የፍርድ ቤት ውሎ ማጠቃለያ ከስር ባለው ሊንክ ላይ ይገኛል፡፡

https://cardeth.org/am/%E1%8B%A8%E1%8D%93%E1%88%88%E1%89%B2%E1%8A%AB-%E1%88%98%E1%89%A5%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A0%E1%88%AB%E1%88%9B%E1%8C%81%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%88%B0/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *