ዶ/ር መረራ ጉዲና በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን መቃወሚያ አስገቡ (ሚያዚያ 16/2009)

በመረራ ጉዲና መዝገብ ለሚያዝያ 16/2009 የተቀጠረው በክሱ ተካተው በሃገር ውስጥ የሌሉ ግለሰቦች እና ሚዲያዎች ጉዳያቸው በሌሉበት እንደሚታይ ከተወሰነ በኋላ፤ 1ኛ ተከሳሽ የሆኑት ዶ/ር መረራ በቀረበባቸው ክሶች ላይ ያላቸውን መቃወሚያ ለመስማት ነው። በዚህ መሰረት ዶ/ር መረራ በጠበቆቻቸው አማካኝነት 11 ገፅ የመቃወሚያ አቅርበዋል። በፅሁፍ የቀረበው መቃወሚያን በችሎት መሰማቱ አስፈላጊ እንዳልሆነ ዳኞች የተናገሩ ቢሆንም፤ ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ችሎቱ ክፍት መሆኑን እንዲሁም ሚዲያዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ወዳጆቻቸው እየተከታተሉ ስለሆነ መሰማት አለበት ብለው በመጠየቃቸው ዳኞቹ 5ት ደቀቂቃ ሰጥተዋቸው በመቃወሚያው ላይ ያለውን ሃሳብ በችሎት አሰምተዋል።

በ1ኛ ክስ ጉዳያቸው በሌሉበት ከሚታየው 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሽ ጋር አንቀፅ 238(1) እና (2) ስር በመተላለፍ የተመለከተውን በመተላለፍ የቀረበውን ክስ በተመለከተ፤ ዶ/ር መረራ ከተጠቀሱት ተከሳሾች ጋር ምንም አይነት ድርጅታዊ ቁርኝት ጉዳይ ባለመኖሩ የቀረበባቸው የክስ ጭብጥ ተነጥሎ እንዲታይ በመቃወሚያው ላይ ተጠይቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 01/2009 አንቀፅ 2(1) ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ለብቻቸው የቀረበባቸውን 3ኛ ክስ በተመለከተ፤ ዶ/ር መረራ ከየትኛውም የሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እና በሽብርተኝነት ከተሰየሙ ድርጅቶች ጋርም ምንም ግንኙነት ኖሯቸው እንደማያቅ ተገልፇል።

የወንጀል አንቀፅ 486(ለ)ን በመተላለፍ  ለብቻቸው የቀረበቸውን 4ኛ ክስ በተመለከተ፤ “የሃሰት ወሬን ለማውራት በማሰብ” በሚል የቀረበው ክስ ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ ጋር የሚያያዝ እንጂ ሃሰተኛ ወሬን መንዛት እንዳልሆነ፤ እንዲሁም በ2006 ተፈፀመ የተባለ ወንጀልን አቃቤ ህግ እድካሁን ድረስ ማስረጃውን ይዞ ማቆየቱ የክሱን እውነትነት እንደሚያጠራጥር በመቃወሚያው ላይ ተጠቅሷል።

ባጠቃላይ በዶ/ር መረራ ላይ የቀረቡት ክሶች በወንጀል ክስ አግባብ መሰረት ተሟልቶ ያልቀረቡ በመሆኑ ሁሉም ክሶች ውድቅ ተደርገው በነፃ እንዲሰናበቱ ተጠይቋል።

አቃቤ ህግ በክሱ መቃወሚያ ላይ ያለውን አስተያየት በፅሁፍ ለመቀበል ቀጣይ ቀጠሮ ለሚያዚያ 26/2009 ቀጠሮ ተይዟል።

ዶ/ር መረራ ያቀረቡት መቃወሚያ ከስር ተያይዟል።

Dr Merera Priliminary Defence April 2017

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *