ዴሞክራሲን ብቸኛው የጫወታ ሕግ ማድረግ! 

 

ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል /ካርድ/)፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011፣ በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መዝገብ ቁጥር 4307 ሐምሌ 17፣ 2011 የተመዘገበ፣ ቦርድ መር፣ የአገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው። ካርድ በሰብዓዊ መብቶች እሴት ላይ የቆመ ዴሞክራሲያዊ ባሕል ያበበባት ኢትዮጵያን የማየት ራዕይ ሰንቆ፥ የኢትዮጵያ ዜጎች እና የዜጎች ማኅበራት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር በመሟገት ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲያሰፍኑ የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ማድረግ ተልዕኮ በማንገብ እየሠራ የሚገኝ ድርጅት ነው። ተጨማሪ ያንብቡ...

 


የካርድ ማንነት

ካርድ በሰብዓዊ መብቶች እሴቶች የታነፀ ግንዛቤ ማሳደግ፣ ማደራጀት፣ እና የፖለሲሲ ሙግት በማድረግ ዴሞክራሲያዊ የብዙኃን ባሕል እና ሕዝባዊ ንቅናቄን ለመፍጠር እየተጋ ያለ ድርጅት ነው። 

የካርድ ራዕይ
በሰብዓዊ መብቶች እሴት ላይ የቆመ ዴሞክራሲያዊ ባሕል ያበበባት ኢትዮጵያን ማየት።  

የካርድ ተልዕኮ
የኢትዮጵያ ዜጎች እና የዜጎች ማኅበራት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር በመሟገት ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲያሰፍኑ የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ማድረግ።


የካርድ አንኳር ዓላማዎች
ካርድ፣ በሕግ የተመዘገበባቸው የሥራ ኃላፊነቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
 

  • በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ባሕል እንዲያብብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መሥራት
  • የሰብዓዊ መብቶች እና የዴሞክራሲ ዕድገት ደረጃን በመከታተል እና በመገምገም መንግሥታዊ የሆኑ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ተጠያቂነት እንዲያዳብሩ ማድረግ
  • የዴሞክራሲ ግንባታን ለማገዝ የሚያስችሉ ተፅዕኖዎችን ለማድረግ የምርምር ሥራዎችን መሥራት፣ የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት፣ እና የማግባባት ሥራዎችን መሥራት
  • ለዴሞክራሲ ተቋማት ቴክኒካዊ እና ሙያዊ ድጋፍ መስጠት
  • ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ የፖሊስ ማቆያዎችን፣ የማረሚያ ቤቶችን አያያዝ እና የፍርድ ቤቶችን ሒደት መከታተል እና መገምገም
  • ምርጫዎችን መታዘብ፣ የዜግነት እና የመራጮች ትምህርት መስጠት

     


Programs